Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የፍቅር ጥግ ኢየሱስ

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኧረ እንዴት ያለ

ምን ዓይነት ፍቅር ነው

ራሱን ለእኔ መስዋዕት ያስደረገው

ኧረ እንዴት አድርጎ እንዴት ቢወደኝ ነው

ራሱን ስለእኔ አሳልፎ የሰጠው

ነቀፋ የሌለበት ንጹህ የእግዚአብሔር በግ

የመላእክት ሰራዊት ወድቀው የሚሰግዱለት

ማስቆም አቅቶት ተገዶ እኮ አይደለም

ራሱን የሰጠው ወዶና ፈቅዶ ነው

ለአእምሮ ይከብዳል

እኔ ይደንቀኛል

ኧረ እንዴት

ኧረ እንዴት

ኧረ እንዴት ያለ

ምን ዓይነት ፍቅር ነው

ራሱን ለእኔ መስዋዕት ያስደረገው

ኧረ እንዴት አድርጎ እንዴት ቢወደኝ ነው

ራሱን ስለእኔ አሳልፎ የሰጠው

ሊመጣ ያለውን አስቀድሞ አውቆ

የደም ላብ አልቦት በልቡ ተጨንቆ

ይለፍ ከእኔ ብሎ ይህ መራራ ፅዋ

ግን ያልከው ይሁን ብሎ ፈቃዱን ያስገዛ

እንዴት ያለ ፍቅር

እንዴት ያለ ጸጋ

ኧረ እንዴት

ኧረ እንዴት

ኧረ እንዴት ያለ

ምን ዓይነት ፍቅር ነው

ራሱን ለእኔ መስዋዕት ያስደረገው

ኧረ እንዴት አድርጎ እንዴት ቢወደኝ ነው

ራሱን ስለእኔ አሳልፎ የሰጠው

በምን ዓይነት መታዘዝ

በምን ዓይነት ፍቅር ነው

የዓለም ፈጣሪ ሁሉን ቻዩ ጌታ

በሸላቾቹ ፊት እንደ በግ ዝም ያለው

እጅግ ይገርመኛል

ኧረ እንዴት

ኧረ እንዴት

የፍቅር ጥግ ኢየሱስ

የፍቅር ልክ ኢየሱስ

ተገብቶኝ ሳለ ሊተወኝ

የወረደ ሊታደገኝ

የፍቅር ጥግ ኢየሱስ

የፍቅር ልክ ኢየሱስ

አልቀረሁም በጭለማ

እርሱ ለእኔ ስለደማ

ኧረ እንዴት ያለ

ምን ዓይነት ፍቅር ነው

ራሱን ለእኔ መስዋዕት ያስደረገው

ኧረ እንዴት አድርጎ እንዴት ቢወደኝ ነው

ራሱን ስለእኔ አሳልፎ የሰጠው

የፍቅር ጥግ ኢየሱስ

የፍቅር ልክ ኢየሱስ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ