አብቃኝ ለኢየሩሳሌም
Abqagn Leyerusalem
2013 · ትራክ 2 · 4:36 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አብቃኝ ለኢየሩሳሌም (፫x) ሕይወቴን
አብቃኝ ለኢየሩሳሌም ሕይወቴን
ቁጥር 1 · Verse 1
በሚያስፈራው ሞገድ በሃዘን ውሽንፍር
መላው ተደናግሮኝ ስተክዝ ስሸበር
ረግረግ ውስጥ ሰጥሜ ጨለማው ሲውጠኝ
ጠብቀኝ ጌታዬ ከጭንቀት አድነኝ
አዝማች · Chorus
አብቃኝ ለኢየሩሳሌም (፫x) ሕይወቴን
አብቃኝ ለኢየሩሳሌም ሕይወቴን
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰይጣን ሲደልለኝ ዓለምን እንዳልክድ
አሽከሩ ሊያደርገኝ ወጥመዱን ሲያጠምድ
በዙሪያዬ ሲዞር ሲያገሳ እንደ አንበሳ
ጠብቀኝ አምላኬ ከዚህ ሁሉ አበሳ
አዝማች · Chorus
አብቃኝ ለኢየሩሳሌም (፫x) ሕይወቴን
አብቃኝ ለኢየሩሳሌም ሕይወቴን
ቁጥር 3 · Verse 3
መርጫለሁ ጌታ አንተን ለመከተል
ዓለምን ንቄአለሁ ለመሸከም መስቀል
መከራውን ችዬ ስለ አንተ ልነቀፍ
በጉዞዬ እርዳኝ ከእንግዲህ አምላኬ
አዝማች · Chorus
አብቃኝ ለኢየሩሳሌም (፫x) ሕይወቴን
አብቃኝ ለኢየሩሳሌም ሕይወቴን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ