Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አጋፔ

Agape

2015 · ትራክ 1 · 5:22 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንድ ጉዳይ አንድ ነገር

ሲወራ ቢዋል ሲተረክ ቢታደር

የማያሰለች እውነት የሆነ

ለዓለም ሁሉ የተከወነ (፪x)

አጋፔ (፪x) ፍቅር ነው እርሱ

ሞተልን ሳይራራ ለነፍሱ

አጋፔ (፪x) ፍቅር ነው እርሱ

ፍቅሩ እጅግ ጥልቅ ነው ንጉሡ

እጆች ገረፉት የፈጠራቸው

ተፉበት ጌታ ላይ መች ፀፀታቸው

ኤሎሄ ኤሎሄ ጩኽቱስ ተሰማ

የዓለሙ ጌታ ሆነ እንደ ደካማ

ንጹህ ሆኖ ሳለ እንደወንጀለኛ

በውርደት ሰቀሉት የሱስን ስለኛ

መለኪያስ አለ ወይ ለዚህ ፍቅር መጠን

እንዲሁ ወዶን እራሱን ለሰጠን

አጋፔ (፪x) ፍቅር ነው እርሱ

ሞተልን ሳይራራ ለነፍሱ

አጋፔ (፪x) ፍቅር ነው እርሱ

ፍቅሩ እጅግ ጥልቅ ነው ንጉሡ

በዚህ ዓለም ፍቅር (፪x)

የወደደውን ማንም ይወዳል

መልካም ላረገ እርሱም ይክሳል

የኢየሱሴ ግን የሚለየው

ራሱን የሰጠ ለጠላ ነው

የኢየሱሴማ የሚለየው

ነፍሱን የሰጠ ለገፋው ነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ