Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
አለኝ ደስ ደስ — ዳግማዊ ጥላሁን

አምላክ እንደሌለው እንደማንም ሰዉ

አይወጣኝም ክፉ ቃልህ ጊዜ አለዉ

እንደመልህቅ ይዞ አይለቀኝም ፍቅርህ

ስጐዳብህ አይቶ ለካ አይችልም ልብህ (፪x)

ጌታዬ በግርማ ሞገስ ጌታዬ ቤቴ ስትደርስ

ጌታዬ ነፍሴን መለስካት ጌታዬ አለኝ ደስ ደስ (፪x)