Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
አልጥልህም አልተውህም — ረዳ አብርሃም

"በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም

ከሙሴ ጋር እንደሆንኩ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ

አልጥልህም አልተውህም ፣ አልጥልህም አልተውህም"

ከሙሴ ጋር እንደነበርኩ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ

ብቻ በርታ ጽና ልጄ ሁሉን መልካም አደርጋለሁ

ምንም ነገር ዓይነካህም እርግማን አይደርስብህም

በጠላት ላይ ትጫማለህ ዘንዶ እባቡን ትረግጣለህ