Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
አምንሃለሁ — ዮሴፍ ካሳ

ሰማዩ ጸጥ አለ ያ ዝናቡ ጠፋ

ዳመናም አይታይ ምንም አያካፋ

ምድርም ጸጥ አለች መሬቱም ደረቀች

ለምልሞ የነበረው ጠውልጐ አለቀ

ሰው ገሸሽ አለ ከቀኝ ከግራዬ

ተስፋ ቢስ አደረጉኝ በዝቶ መከራዬ

አሁን ተሳሳቱ መች እንዲህ ልቀር

በጊዜው ይመጣል ተስፋ የእግዚአብሔር