Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንድነት

Andinet

2016 · ትራክ 2 · 5:00 · አማርኛ · አምልኮ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ወንድሞች በአንድነት ሲቀመጡ

እነሆ መልካም ነው እነሆ ያማረ ነው

እንደ አሮን ራስ ላይ እንደሚወርድ ዘይት

በረከት ይፈስሳል በአንድነት ላይ

አንድ እንሁን አንድ እንሁን

ጌታ እንደ ጸለየው

አንድ እንሁን አንድ እንሁን

ዓለም እንዲያምን

ልዩነት ቢኖረን አንከፋፈልም

አንድ አካል ነን በክርስቶስ

እያንዳንዳችን ብልቶች ነን

እርስ በእርስ እንተሳሰብ

አንድ እንሁን አንድ እንሁን

ጌታ እንደ ጸለየው

አንድ እንሁን አንድ እንሁን

ዓለም እንዲያምን

ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ