Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
አንተው ትሻለኛለህ — አስቴር ዮሴፍ

የንጉሥ ልጅነት እንቢ ያለ

ግብፅንም በእምነት የተወ

ሳያየው እንደሚያየው ቆጥሮ

ብድራቱን አይቶ አሻግሮ

ምንም እንኳን የግብፅን ጥበብን ቢማርም

ሙሴ የባእድ ዕውቀት ከቶ አልማረከውም

ከገንዘብም ይልቅ መከራን መረጠ

ስለ ሥምህ ለአንተ መነቀፍን ወደደ