Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
አያምረኝም — ቴዎድሮስ ታደሰ

ለእኔስ ሕይወት በዝቶልኛል ፣ ሕይወት በዝቶልናል

ኢየሱሴ መዳኛ ማምለጫም ሆኖኛል

ኢየሱሴ መዳኛ ማምለጫም ሆኖኛል (፪x)

ሰው ሁሉ እንደመሰለው ቢያወራ ብዙ ቢናገር

ለእኔ ግን የገባኝ እውነት አረገኝ በዚያው እንድቀር

ለዚህ ነው እምቢ ማለቴ ሳይገደኝ ወጣትነቴ

የዓለምን ግብዣዋን ንቄ ወገቤን ትጥቄን ማጥበቄ