Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
የፍቅርህ ባለ ዕዳ — ይድነቃቸው ተካ

የደህንነቴ መደምደሚያ

የክብር ስሜ ነህ መጠሪያ

ማዕረጌ ሆነህ በሞትህ

እኔም ተባልኩኝ ልጅህ (፪x)

የሞትህ ፍሬ የድካምህ

በጣር የወለድከኝ ልጅህ

በመከራ አልፈህ ያገኘኀኝ

የዕንባህ ልጅህ ነኝ (፪x)