Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
በገናውን — ዳንኤል አምደሚካኤል

በገናውን እጄ እየደረደረ

አፌም ምህረትህን እየተናገረ

መንፈሴና ነፍሴ በአንድነት:ተስማምተው

ያመሰግኑሃል ጌታ ክበር ብለው ኦሆሆ

በምሥጋና የተፈራህ በአምልኮ ኦሆሆ

አምላኬ ሆይ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ (፪x)

የለም እኮ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ

የለም እኮ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ