በል እፈር ጠላቴ
Bel Ifer Telate
7:23 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የመጎብኛዬ ወራት ሲመጣ
ለሚፈሩህ የጽድቅ ፀሐይ ደግሞ ሲወጣ
ፀሎቴም ተሰማ
ጠላት እየሰማ
ዕዳዬ ተከፈለ
ከሳሼ የታለ
ጉልበቴ በረታ
በኢየሱስ ጌታ
አዝማች · Chorus
በል እፈር ጠላቴ እዳዬ ተከፍሏል
ከየት ታምጣ ከሳሼ ቀንበሬ ተሰብሯል
በነጻነት ልኖር ነጻ አውጥቶኛል
ዳግም ላልታሰር ኤፍታ ብሎ ለቆኛል
ክብር ለስሙ ይሁን
ክብር ላዳነኝ ይሁን
ክብር ለጌታ ይሁን
ክብር ላየሱስ ይሁን
ቁጥር 2 · Verse 2
1.ዝናብም ባይኖር ነፋስም ባላይ
ድል አውጃለሁ ባዶ ተስፋ ላይ
ደረቁ ምድር ይለመልማል
በባዶ ጉድጓድ ዉሃ ይሞላል
ያለቀው ነገር ሞልቶ ይፈሳል
የተጠማ ሁሉ ጠጥቶ ይረካል
ቁጥር 3 · Verse 3
2.ምንም ቢበዛ የኔ መከራ
ከቶ ቢጎድል የወይራ ሥራ
ያዳነኝ ጌታ ሀይል ይሆነኛል
እንደ ዋላ እግሬን ያበረታኝል
ጠባቂዬ የሱስ አቅም ይሆነኛል
በከፍታ ላይ ያራምደኛል
ቁጥር 4 · Verse 4
3.ያመንኩት ወዳጅ ቢከዳ እንኳን
ቢፈርስ ቢበተን ምድራዊ ድንኳን
የታመንኩ ጌታ ከኔ ጋር ያለው
ያረጀውን ነገር አዲስ ጀመረው
ማይከዳ ወዳጅ ከጎኔ ያለው
የታሪክ መዝገብ አገላበጠው
ያመንኩት የሱስ ከኔ ጋር ያለው
የሞትን አዋጅ ገለባበጠው
ቁጥር 5 · Verse 5
4.ሞቶ ተቀብሮ ቢሸት ነገሬ
አንድም ባይሰማ አስደሳች ወሬ
ወድቆ አይቀርም በከንቱ ሞቶ
ሕይወት ይዘራል ጌታዬ መጥቶ
ትንሣኤ አለ ዛሬም ካባቴ
በእግሩ ቆሟል እፈር ጠላቴ
አዝማች · Chorus
በል እፈር ጠላቴ ብወድቅ እነሳለሁ
ቢጨልምብኝ..ም ብርሃን እወጣልሁ
ወደ እግዚአብሔር እመለከ..ታለሁ
መድኃኒቴን አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ
እሱም ይሰማኛል ጽድቅን ያሳየኛል
እሱም ያደምጠኛል ዕረፍት ይሰጠኛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ