Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በቂ ነህ

Beqi Neh

2002 · 4:52 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

“እግዚአብሔር በቂ ነህ”

በሐረር አማኑኤል ኅብረት ኳዬር

(እግዚአብሔር) 2

(በቂ ነህ ከበቂም በላይ) 2 በቂ ነህ

ምን ጎሎብህ ምን አጥተህ

ሁሌ ሙሉ አይጎልህ

(ሁሉ በእጅህ ነው በደጅህ) 2

ስጦታህ ብዙ ነው ማንም አይመስልህም

ሁሌ ትሰጣለህ ከቶ አይጎልህም

ሰረገላዎችህ የብዙ ሺህ ናቸው

እጅህ ሰፊ ጌታ ሥራህ እጅግ ድንቅ ነው

ተትረፍርፈህ ጌታ ታትረፈርፋለህ

ሁሉ ያንተ የሆንህ (የሁሉ አምላክ ነህ) 2

(እግዚአብሔር) 2 ……

አለሁ የሚል ከቶ በችግር የሚደርስ

በመከራ ፈንታ ደስታን የሚክስ

ሊረዳ የሚተጋ ወገብ አሸንፍጦ

ሁሌ የሚያሰማራ እጅጉን አስፍቶ

ሁሉ በጠፋበት አንተ ብቻ አለህ

ጌታዬ ግን በቂ (ከበቂም በላይ ነህ) 2

(እግዚአብሔር) 2 ……

ሁሉ ከእጅ ጠፍቶ የሚያዝ ባይኖርም

ዙሪያ ገባው ባዶ ጨለማ ቢሆንም

እርሻ መብልን ባይሰጥ ከብቶችም ባይኖሩ

ወይንና በለስም ፍሬ ባያፈሩ

አንተ ግን ብቻህን ታደላድላለህ

በቂ ነህ ጌታዬ (ሃሳብ ታስጥላለህ) 2

(እግዚአብሔር) 2 ……

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ