Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
እግዚአብሔርን መምሰል — ጌታያውቃል ግርማይ እና ብሩክታዊት አሰፋ

ለሥጋዊ ነገር እራስን ማስለመድ

ከእግዚአብሔር ሀሳብ እርቆ መራመድ

ለጊዜያዊ ደስታ ነፍስን አስገዝቶ

ዛሬን ብቻ መኖር የነገውን ትቶ

አይጠቅመኝም ከቶ ይህን አውቄዋለሁ

እግዚአብሔርን መምሰል ለእኔ ማትረፊያ ነው

ብዬ ተናግሬ ጉዞ ጀምሬያለሁ

ጥማቴም ናፍቆቴም ጌታዬን መምሰል ነው