Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
እኔም ልወቅህ ዛሬ — ነጻነት አሰፋ

ነፍሴ የአምላክሽን ክብር እይ ታላቅነቱ ይግባሽ

ጌታ መሆኑን ተረጂ ወደ እርሱ ይሁን ልብሽ

ቸል አትበይ አትርሺ በዙፋኑ የተቀመጠውን

እንደሚገባሽ አክብሪው ማራኪሽ እርሱ ይሁን

እኔም ልወቅህ ዛሬ ልወቅህ እንደሚገባኝ

በፊትህ ልስገድልህ ክብርህን ጌታ አሳየኝ