እረኛዬ
አማርኛ
አዝማች · Chorus
እረኛዬ
ማረፊያዬ
ቃልህን ስትናገር
ልብን ያሳርፋል
የምትመክረው ምክር
ተስፋን ያሳድራል
ሆነህ አይቼሃለሁ
ልቤ አንተን ወዶሃል
ቁጥር 1 · Verse 1
አይከፋኝም አባ ለዚያ አትስጋ
ምን ጎደለው አንተን የተጠጋ
መተማመን መጏደድ ባንተ ነው
ሁሉ ባለህ ሁሉን በፈጠርከው
አይኖችህም በምድር ላይ ያያሉ
ከኔው ጋራ ይንከራተታሉ
ሆድ ሲብሰኝ ከላይ ትወርዳለህ
በደመናት ትረማመዳለህ
አዝማች · Chorus
እረኛዬ
ማረፊያዬ
ቃልህን ስትናገር
ልብን ያሳርፋል
የምትመክረው ምክር
ተስፋን ያሳድራል
ሆነህ አይቼሃለሁ
ልቤ አንተን ወዶሃል
ቁጥር 2 · Verse 2
የገባሀውን ቃል ኪዳን አትረሳም
የሰጠህውን ተስፋ አታጠፋም
ሌትና ቀን ሁሌ ትተጋልህ
እንዲፈጸም ቀኑን ታፈጥናለህ
ይህን ላደርግ ኃይሌ እንዲህ አነሰ
ብለ አትመጣም ጉልበቴም ደከመ
በአንተው ምለህ መች እንዲ ይሆናል
ችሎታህ ሁሌ ያስተማምናል
አዝማች · Chorus
እረኛዬ
ማረፊያዬ
ቃልህን ስትናገር
ልብን ያሳርፋል
የምትመክረው ምክር
ተስፋን ያሳድራል
ሆነህ አይቼሃለሁ
ልቤ አንተን ወዶሃል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ