ኢየሱስ
Eyesus
2009 · ትራክ 1 · 6:21 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ብዙ ማስጨነቅ በብዙ ማሸበር
ዙሪያዬን ሲዞሩ (፫x)
በአንድ መንገድ መጥቶ በታናቸው
አየሁ በሰባት መንገድ (፫x)
እጆቼኔም አልሰጥም ወጀቡን አይቼው
ማዕበሉን ፈርቼው (፪x)
ከእነርሱ ጋር ካለው ከእኔ ጋራ ያለው
ይበልጣል አምናለሁ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ልቤ በእርሱ ላይ በጅግናው ጌታ
ፎክሮበታል እንደማይረታ
ሁሉም ቢናገር የስንፍና ቃል
ጐልያድ እንደድምቅ የማይቀር ነው
ልቤ በእርሱ ላይ በጅግናው ጌታ
ፎክሮበታል እንደማይረታ
ሁልም ቢናገር የስንፍና ቃል
ዮርዳኖስ እንደሚከፈል የማይቀር ነው
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ የእኔ መመኪያ ነህ
ኢየሱስ የእኔ ማረፊያ
ኢየሱስ የማምለጫ ዓለት
ኢየሱስ ከጠላት ወጥመድ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፈርዖን ለምን ነው
መቸኮሉ ኃይሉን መጨረሱ (፫x)
በእግዚአብሔር ህዝብ ላይ
በትዕቢት ተነስቶ አንዲህ መገስገሱ
ለፍቶ ደክሞ አያውቅም
የሕዝቡ ጠባቂ የህዝቡ መከታ
ባህር ተከፈለ ሕዝቡም ተሻገረ
ፈርዖን ቀረ እዚያ
የእስራኤል አምላክ የእኔም ኣምላክ ነው
ወጥመድ ተሰብሮ ስንቴ አምልጫለሁ
ጠላት ፊቴ መቆም አይችልም
የሚጠብቅኝ የሚተኛ አይደለም
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ የእኔ መመኪያ ነህ
ኢየሱስ የእኔ ማረፊያ
ኢየሱስ የማምለጫ ዓለት
ኢየሱስ ከጠላት ወጥመድ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ኢየሱስ የነፍሴ ከላላ
ኢየሱስ የለኝም ከአንተ ሌላ
ኢየሱስ የማምለጫ ዓለት
ሆንከኝ ለእኔ አባት
ቁጥር 5 · Verse 5
ከእናቴ ማህፀን ለራሱ የለየኝ ለክብሩ የቀባኝ
ተስፋ አስጨብጦኛል በመንገዴ ላይ ገብቶ
ለአፍታ አንደማይተወኝ
ድምጹን እየሰማሁ እከተለዋለሁ ከኋላው አሮጣለሁ
ወደ ታየለኝ ግብ አልቀርም እደርሳለሁ ዘልቄ እገባለሁ
ተስፋን የሰጠው የታመነ ነው
መቼ እንደ ሰው ቃሉ ሊሽረው
ወጥመዴን ስብሮ ያሻግረኛል
የጠላቶቼን ደጅ ያወርሰኛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ