ኢየሱስ ያድናል
Eyesus Yadnal
2019 · 5:34 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከላይ ወርዶ ለኛ ስለሞተው
የተነሳው ደግሞም የሚመጣው
የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ
እርሱ ብቻ ነው ከሞት የሚያድነው
በእርሱም አምነን ከጥፋት ድነናል
የዘላለም ህይወት አግኝተናል
ከሚያምኑት ከቅዱሳን ጋራ
የመንግስቱ ወራሾች ሆነናል
ቁጥር 2 · Verse 2
በልጁ በኢየሱስ ያመነ ህይወት አለው
ማንም በእርሱ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው ፬x
ያለ ጌታ ኢየሱስ አማላጅነት
ዓለም ሁሉ ሊደን በጭራሽ አይችልም
እውነት መንገድ ህይወት እርሱ ነውና
ወደ አብ መድረሻ ሌላ የለም
መዳን ከእርሱ በቀር በማንም የለም
ለአለም ሁሉ የሞተው ኢየሱስ ብቻ ነው
እንድንበት ዘንድ ለኛ የተሰጠን
የናዝሬቱ የእየሱስ ስም ነው
አዝማች · Chorus
እየሱስ ያድናል
ከሲኦል ገሃነም እሳት
እየሱስ ያድናል
ከጨለማው ዘላለም ሞት
እየሱስ ያድናል
ያድናል ይታደጋል
እየሱስ ያድናል
ህይወትን ይሰጣል
ቁጥር 3 · Verse 3
ከላይ ወርዶ ለኛ ስለሞተው
የተነሳው ደግሞም የሚመጣው
የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ
እርሱ ብቻ ነው ከሞት የሚያድነው
በእርሱም አምነን ከጥፋት ድነናል
የዘላለም ህይወት አግኝተናል
ከሚያምኑት ከቅዱሳን ጋራ
የመንግስቱ ወራሾች ሆነናል
ቁጥር 4 · Verse 4
በልጁ በኢየሱስ ያመነ ህይወት አለው
ማንም በእርሱ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው ፬x
ማንስ ለማን በእርሱ ፈንታ እሞታለሁ
ብሎ የራሱን ነፍስ አሳልፎ ይሰጣል?
ያለ ሀጥያቱ የሌላውን ሀጥያት
ለራሱ ወስዶ ማን ይሸከማል?
እየሱስ ግን ራርቶ ይህን አደረገ
እኛ ነፃ አወጣን ለሁላችን ሞቶ
ከሰማያት ወርዶ ዝቅ ዝቅ አለ
አምላክነቱን ክብሩንም ትቶ
አዝማች · Chorus
እየሱስ ያድናል
ከሲኦል ገሃነም እሳት
እየሱስ ያድናል
ከጨለማው ዘላለም ሞት
እየሱስ ያድናል
ያድናል ይታደጋል
እየሱስ ያድናል
ህይወትን ይሰጣል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ