Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍቅርህ ነክቶኛል

Feqreh Nektognal

ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፍቅርህ ነክቶኛል ምን አረጋለሁ

እጄን ዘርግቼ አመልክሃለሁ (፪x)

ምን አይነት ፍቅር ነው አየቼ ማላውቀው

እግዚአብሔር ለኔ በልጁ የገለጸው

በአስደናቂው ፍቅርህ የባረካት ነፍሴ

እጀግ ወዳሃለች ተመስገን ኢየሱሴ

ፍቅርህ ነክቶኛል ምን አረጋለሁ

እጄን ዘርግቼ አመልክሃለሁ (፪x)

የተወደደች ቀን አንተን ያወኩባት

እንደምን ያቺ ዕለት የተባረከች ናት

መደነቄ በዝቷል ካወኩህ ጀምሮ

ይቆጨኝ ነበረ ያንተ ባልሆን ኖሮ

ፍቅርህ ነክቶኛል ምን አረጋለሁ

እጄን ዘርግቼ አመልክሃለሁ (፪x)

በፊትህ ደስታ በመገኘትህ

ደስ የምታሰኘኝ አምላኬ አንተ ነህ

የፍቅር ትርጉሙ የገባኝ ባንተ ነው

ከማመስገን በቀር የምልህ ምንድን ነው

ፍቅርህ ነክቶኛል ምን አረጋለሁ

እጄን ዘርግቼ አመልክሃለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ