Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ፍቅሬን አስቀድማት — አዲሱ ወርቁ

ሌት ከቀን ደክሜ ስምህን ለማስከበር

ብዙ ተጉዣለሁ ወንጌልን ለማብሰር

አምላኬ እንዲህ ይላል እያልኩኝ ተግቼ

ድምጼ እስከሚሰልል ነፍሳት ተጣርቼ

አንዳንዴ ጉዳትን አንዳንዴም ማጣትን

ስለ ስሙ ችዬ በለቅሶ ያለፍኩትን

ሁሉንም ዘርዝሬ ታሪኬን ስገታ

አምላኬ እንዲህ አለኝ በረቂቅ ዝግታ