Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ጌታዬን አከብራለሁ — አዲሱ ወርቁ

አነባ ጌታዬ አፈር ላይ ተደፍቶ

የወደቀበትን ጭንቀት ተመልክቶ

ጌታዬ ተጨንቆ አባዬ ሆይ አለ

አጋዥ አልተገኘም ለጌታ የዋለ

መስቀል ተሸክሞ ትከሻው ተላጠ

ግርፋቱ በዛ ገላዉ ተመለጠ

ራቁቱን ደም ሲያፈስ በቀራንዮ ዋለ

አንገቱ ደፋ ሲል ዕዳ ተከፈለ