Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ህዝብህን አብዛህ — ተስፋዬ ጋቢሶ

ዓላማ ይዞ የተሰለፈ የሚያስፈራ የአንተ ሰራዊት

ጠላትን ሁሉ እያሸነፈ በአንተ መሪነት ቀንና ሌሊት

ባሕር ተሻግሮ በምድረበዳ ጊንጡን ረጋግጦ

ጥቂቱ ሕዝብህ ከአንተ ጋር በዝቶ ርስቱን ጨበጠ ከብዙ በልጦ