Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ክበር እላለሁ — አዜብ ኃይሉ

ነግቶ እስከሚመሽ መሽቶም እስኪነጋ

ስላንተ ብጫወት ስላንተ ባዎጋ

እኔ አይሰለቸኝም አልታክትም ከቶ

ምላሴም አይደክም ፍቅርህን አውግቶ

አመሰግናለሁ ደግሜ ደግሜ

እጅግ በገነነው ዙፋንህ ሥር ቆሜ