Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ክብርህ ሽልማቴ — ይድነቃቸው ተካ

ሰማይና ምድርን አጸና በቃሉ

ምድርና ሞላዋን ሸፈነ በክብሩ

ዐይኑን ከፍቶ ያየ እንዴት የታደለ

የእግዚአብሔርን ጥበብ ክብሩን ያስተዋለ

ሰማዩም ይናገር ምድሩም ይመስክር

የግርማ ሞገሱን የውበቱን ንገር

ሁሉን የፈጠረ ሁሉንም የሰራ

ከእርሱ በቀር ማነው አዬ እስቲ ይናገራ