Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ክቡር ስሙን

Kibur Simun

2024 · ትራክ 2 · 4:55 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምህረቱ ፍቅሩ በዝቶልኝ ነው

ኦ በደስታ ፊቱ ምዘምረው/2

ጌታ እየሱስ እጄን ይዞኛል መኖሪያዬን እርሱ ነው

የመንፈሱን ደስታ ሰቶኛል ፊቱ ልቅረብ ላምልከው

ኦ ዘውትር ክቡር ስሙን ልጥራው/2

ስሙ ድንቅ ነው ጌታ ዘላለም የከበረ

በሰማይም በምድር እጅጉን የደመቀ

አዕላፍ ይጠሩታል በፍቅሩ ያዳናቸው

ጌታ እየሱስ የሚለው ስም መድሃኒት የሆናቸው

ኦ ስሙ ይክበር ከስሞች ሁሉ በላይ ነው

ከሱ ሌላ ደህንነትን መሻት ዘበት ነው

በደስታ ደጋግሜ የጌታዬን ስም ልጥራው

በደስታ ደጋግሜ የእየሱስን ስም ልጥራው

ምህረቱ ፍቅሩ በዝቶልኝ ነው

ኦ በደስታ ፊቱ ምዘምረው/2

ጌታ እየሱስ እጄን ይዞኛል መኖሪያዬን እርሱ ነው

የመንፈሱን ደስታ ሰቶኛል ፊቱ ልቅረብ ላምልከው

ኦ ዘውትር ክቡር ስሙን ልጥራው/2

እግዚአብሔር አብ እጅጉን ከፍ ከፍ አደረገው

ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው

ጉልበት ሁሉ ለጌታ ለእርሱ ይንበረከካል

ምላስ ለልዑል ክብር ጌታ ነው እየሱስ ይላል

ኦ ሃሌሉያ ስግደት ይገባዋል ለንጉሱ

የተበዣቸው ምስጋናን ዘመሩ በመቅደሱ

በማደሪያው በህዝቡ መሃል ጌታን እያወደሱ/4

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ