Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ኩራት ኩራት አለኝ — ተከስተ ጌትነት

ብርቱ ተብሎ ታምኖበት ልብም በእርሱ ላይ ተጥሎ

አለልኝ ለእኔ እያለ መኖር ሲመኝ ተዘልሎ

የተደገፈው ሸንበቆ መሆኑን እንዲያው ሳያውቀው

ድንገት ተሰብሮ ወደቀ የዚያ ሰው መተማመኛው

አኔማ/እኔ ግን በላዬ ላይ ንጉሴን ሾሜያለሁ

አልፈራ አልደነግጥ በክንዱ እኮራለሁ (፪x)