ላመሰግንህ
Lameseginih
ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሚስኪኑን ፥ ጠራኀኝና ፥ እና ኣበሳን ከእኔ ኣራክና
ኣፌን ለምስጋና ከፈትከው ስለዚህ አዘምራለው
ውድቀቴን ለፍጥረት ሊያውጅ መለከቱንም ሲያዘጋጅ
በጠላቴ ፊት ቀባኀኝ ከፍታውን አስረገትከኝ
አዝማች · Chorus
ላመሰግንህ ተራው ከደረሰኝ መቆዘም ቀርቶ ዘመን ከመጣልኝ ፦
ቁጥር 2 · Verse 2
ከፍታን መውረስ ባንተ ከሆነለኝ እጆቼን ላንሳ ጌታ ክበርልኝ (፭) ፦
ቁጥር 3 · Verse 3
መቆዘም ከእንግዲህ ቀረ ጠላቴም ይኸው አፈረ
በኮረብታ ላይ ቆሜአለሁ ምስጋናዬን አሰማለሁ
ተራሮችም አስተጋቡ ምስጋናዬንም አጀቡ
እናንተንም ከእኔ ጋራ ዘምሩ ስራው ይውራ
ቁጥር 4 · Verse 4
ላገለግልህ ተራው ከደረሰኝ መቆዘም ቀርቶ ቃልህ ከመጣልኝ፦
ከፍታን መውረስ ባንተ ከሆነልኝ አጆቼን ላንሳ ጌታ ክበርልኝ (፭)፦
ቁጥር 5 · Verse 5
ገበታ ተዘጋጀልኝ ረሃቤንም እረሳሁኝ
ጽዋዬም የተረፈ ነው ዛሬ ለሌሎች ሆኛለሁ(፪)
አዝማች · Chorus
ላመሰግንህ ተራው ከደረሰኝ መቆዘም ቀርቶ ዘመን ከመጣልኝ፦
ቁጥር 6 · Verse 6
ከፍታን መውረስ ባንተ ከሆነልኝ አጆቼን ላንሳ ጌታ ክበርልኝ (፭)፦
ቁጥር 7 · Verse 7
ባለቀሱኩባቸው ቀኖች ፈንታ ደስታ ሆኖልኛል ባንተ ጌታ (፫)
በቆዘምኩባቸው ወራት ፈንታ እረፍት ከበበኝ የእኔ ጌታ (፫)
ውድቀቴን በሚሻ ጠላቴ ፊት እራሴን ቀባኸው በዘይት (፫)
ዛሬም ላመስግንህ በደስታ ስራዬን ሰርተሃል ጌታ (፬)
ቁጥር 8 · Verse 8
ላመሰግንህ ተራው ከደረሰኝ መቆዘም ቀርቶ ዘመን ከመጣልኝ
ከፍታን መውረስ ባንተ ከሆነልኝ አጆቼን ላንሳ ጌታ ክበርልኝ (፭)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ