ላምጣልህ ምሥጋና
Lamtaleh Mesgana
2013 · ትራክ 1 · 6:49 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ልትሰራ አስበህ ስትመጣ ወደ እኔ
አንተ ያየኸውን ስታሳየኝ በዓይኔ
ምህረትህ ሲለየኝ ለከበረው ሥራ
ውስጤ ተደነቀ መገረም ተሞላ (፪x)
ቆይ ምኔን ደስ ብሎ የቱስ እኔነቴ
ወደ እኔ ያመጣህ ልታሰገባህ ወደ እኔ
ይሄ አልበቃህ ብሎ በክብርህ እንድትሰራ
ፍቅርህ የመረተኝ ባንተው እንድጠራ
አዝማች · Chorus
ላምጣለህ ምሥጋና ልጨምር ዝማሬ
ሕይወቴን ላዳንከው ከጨካኙ አውሬ
ላምጣልህ ጭብጨባ ልጨምር ውዳሴ
ለክብርህ ትዘምር ከሞት ተርፋ ነፍሴ
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍቅር ግድ ብሎህ እንዲሁ የወደድከኝ
ለሹመት ለክብር ብለህ የወሰንከኝ
ኃጢአት ያጠፋህ ድካሜን የሻረከው
ውልታህ በዝቶብኝ ፊትህ መጥቼአለሁ
ይኸው አድናቆቴ ለክብርህ ምሥጋና
ይኸው መገዛቴ ወደኸኛልና
ይኸው ምሥጋናዬ የከንፈሬ ፍሬ
ኧረ የአንተን ፍቅር ነው ያበቃኝ ለዛሬ
ልትሰራ አስበህ ስትመጣ ወደ እኔ
አንተ ያየኸውን ስታሳየኝ በዓይኔ
ምህረትህ ሲለየኝ ለከበረው ሥራ
ውስጤ ተደነቀ መገረም ተሞላ (፪x)
አዝማች · Chorus
ላምጣለህ ምሥጋና ልጨምር ዝማሬ
ሕይወቴን ላዳንከው ከጨካኙ አውሬ
ላምጣልህ ጭብጨባ ልጨምር ውዳሴ
ለክብርህ ትዘምር ከሞት ተርፋ ነፍሴ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ ሆይ በመንፈስህ እንጂ መች በብርታቴ
ጌታ ሆይ እስካሁን የሆነው በሕይወቴ
ጌታ ሆይ ሠላም ይሰማኛል ነገዬን ሳሰበው
ጌታ ሆይ እንደ በፊቱ አልሰጋም ተስፋዬ ፍቅርህ ነው
አዝማች · Chorus
ላምጣለህ ምሥጋና ልጨምር ዝማሬ
ሕይወቴን ላዳንከው ከጨካኙ አውሬ
ላምጣልህ ጭብጨባ ልጨምር ውዳሴ
ለክብርህ ትዘምር ከሞት ተርፋ ነፍሴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ