Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ለብቻዬ

Lebechayie

2015 · ትራክ 1 · 6:37 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ባለህ ያልኩት ለታ መች ከጐኔ ሆኗል

የቅርቤ ይህ ነው ያልኩት እንዳላየኝ አልፏል

ግን አንድ አለ ወዳጅ ሁሉም ሲሄድ ከእኔ

ያኔ ለብቻዬ ሆነልኝ ከጐኔ

ለብቻዬ (፪x)

አልተውከኝም እኔን ለብቻዬ

ለብቻዬ (፪x)

መች ተውከኝ እኔን ለብቻዬ

ፍቅሩ ጤዛ አይደለም የማለዳ ብቻ

አይገኝለትም መውደዱ ዳርቻ

ፀሐይ አዘቅዝቃ ዋ እኔ ዋ እኔ እያልኩኝ

ያኔ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ አልራቀኝ

ወዳጅ ለእኔስ ወዳጅ

ወዳጅ ሆነህልኛል

ልቤን ሀዘን ጐድቶት

ደርሰህ አጽናንተኸኛል (፪x)

ባለህ ያልኩት ለታ መች ከጐኔ ሆኗል

የቅርቤ ይህ ነው ያልኩት እንዳላየኝ አልፏል

ግን አንድ አለ ወዳጅ ሁሉም ሲሄድ ከእኔ

ያኔ ለብቻዬ ሆነልኝ ከጐኔ

ለብቻዬ (፪x)

አልተውከኝም እኔን ለብቻዬ

ለብቻዬ (፪x)

መች ተውከኝ እኔን ለብቻዬ

የወጠኑት ሳይሆን የያዙት ሲጠፋ

ልብን ያሳዝናል ያስቆርጣል ተስፋ

ግን ኢየሱስ አለ የማይጥል የማይረሳ

ሁሉም መልካም ሆኗል ከእርሱ የተነሳ

ወዳጅ ለእኔስ ወዳጅ

ወዳጅ ሆነህልኛል

ልቤን ሀዘን ጐድቶት

ደርሰህ አጽናንተኸኛል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ