ልጅ ሰጥተኸኛል
Lej Setehegnal
2010 · ትራክ 1 · 4:11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው [1]
በጐ ስጦታና ፍፁም በረከት
ከላይ ከብርሃናት አባት ዘንድ ይወርዳሉ [2]
አዝማች · Chorus
ልጅ ሰጥተኸኝ አባት ልታደርገኝ
የራስህን ፍቅር ልታስተምረኝ
ገባኝ ነገሩ ውሎ ሳያድር
ቀላል አይደለም ነው ታላቅ ሚስጥር
ቁጥር 2 · Verse 2
የአምላክ ስጦታ ልዩ በረከት
በእናት ሆድ ተዋህዶ አጥንትና አጥንት
ከሰው ሰው ስትፈጥር አንተ ለአንተ ክብር
ከአይምሮ በላይ ነው ያሰኘኛል ተዓምር
አዝማች · Chorus
ልጅ ሰጥተኸኝ አባት ልታደርገኝ
የራስህን ፍቅር ልታስተምረኝ
ገባኝ ነገሩ ውሎ ሳያድር
ቀላል አይደለም ነው ታላቅ ሚስጥር
ቁጥር 3 · Verse 3
ተቀብያለሁ የእኔን ስጦታ
የሰጠኸኝን በረከት ጌታ
እንደ ወደድከኝ አየወደድኩህ
ቤትህ እኖራለሁ እያመለኩህ
እግዚአብሔር ያያል ጸሎቴን ይሰማል
በባዕድ ምድር ላይ ፍሬያማ ያደርጋል
በጐ ስጦታና ፍፁም በረከት
ከአንተ ዘንድ ለእኔ ሆኗል የእኔ አባት
አዝማች · Chorus
ልጅ ሰጥተኸኝ አባት ልታደርገኝ
የራስህን ፍቅር ልታስተምረኝ
ገባኝ ነገሩ ውሎ ሳያድር
ቀላል አይደለም ነው ታላቅ ሚስጥር
ቁጥር 4 · Verse 4
ተቀብያለሁ የእኔን ስጦታ
የሰጠኸኝን በረከት ጌታ
እንደ ወደድከኝ አየወደድኩህ
ቤትህ እኖራለሁ እያመለኩህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ