ሊቀ ካህኔ
Liqe Kahine
አማርኛ
×2
ከህይወት ርቄ በዘለዐለም ሞት
ሆኜ በጨለማ ብርሀን በሌለበት
ተጨንቄ ሳለሁ በሀጥያት ሞት ፍርሀት
የሱስን አገኘው ሳለው በእስራት
ምላሽ · Refrain ×2
ከዳዊት ዘር የመዳን ቀንድ ተነስቶልኝ
ለህይወትም ታላቅ ግብዣ ተጋበዝኩኝ
በእግዚአብሔር ፊት እንድቆም ልብስ ሆነልኝ
አብ በልጁ በኢየሱስ ተቀበለኝ
አዝማች · Chorus ×2
ዳግም ላይገባ አንድ ጊዜ ቀርቧል
ሊቀ ካህኔ ስለ እኔ ታርዷል
የሀጥያት ፍርሀት ከእንግዲህ የለም
ጌታ ኢየሱስ ይክበር ዘላለም
ድኅረ አዝማች · Post-Chorus ×4
ጌታ ኢየሱስ ይክበር ዘላለም
መግቢያ · Intro ×2
ሀጥያት የማያውቀው ውዱ የእግዚአብሔር ልጅ
ስለ እኔ ታመመ በፈጠራቸው እጅ
በመስቀል ላይ ሞቶ ስርየት አመጣ
ሲኦል ተሸነፈ ሞትም አቅም አጣ
ምላሽ · Refrain ×2
ይቺ ነፍሴ ይህን መዳን ቸል አትልም
ጎልጎታን ቀራንዮን አላቀልም
ቤዛዬ እና መድሀኒቴ እልሀለው
ከማያልቅ የዘላለም ሞት አምልጫለው
አዝማች · Chorus
ዳግም ላይገባ አንድ ጊዜ ቀርቧል
ሊቀ ካህኔ ስለ እኔ ታርዷል
የሀጥያት ፍርሀት ከእንግዲህ የለም
ጌታ ኢየሱስ ይክበር ዘላለም
ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ