እፈልግሀለሁ
Lord I need you
ትራክ 1 · 6:59 · አማርኛ
አንተ የልቤ ረሃብ የነፍሴ ጥማት
ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት
ከምትገኝበት
በመቅደስህ ሆነህ ሁሌ አስብሀለሁ
ደስ የሚያሰኘውን ፊትህን እሻለሁ
እፈልግሀለሁ
እንደምትናፍቅ ዋላ ወደ ውሀ
አግኝታህ እስክትረካም ከዛ በበረሀ
ምንም አይታያት ማንም አያስቆማት
እንዲሁ አምላኬ ነው የነፍሴ ጥማት ፪x
አገኘሁ እና ጥሜን አረካኸው
ግን ደግሞ እርካታዬ አንተን ሚያስናፍቅ ነው
አሁንም አሁንም ልቤ ይፈልግሀል
በነገሮች መሀል ሀሳቤ ይወሰዳል
ወደ አንተ ይሄዳል
አንተ የልቤ ረሃብ የነፍሴ ጥማት
ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት
ከምትገኝበት
ዋና የልቤ ትኩረት የዓይኔ ደግሞ ፍዘት
የጆሮዬ ጉጉት ድምፅህን ለመስማት
በእጅህ ለመነካት
ረሃቤ ክብርህ ነው ውበትህ ጥማቴ
በሰማዩ ስርዐት ተወስዷል መሻቴ
የምድርን ግሳንግስ ትቼ ወደ ኋላ
ወደ አንተ እሮጣለሁ ዘወትር እንድሞላ
ረሃቤ ነህና
አንተ የልቤ ረሃብ የነፍሴ ጥማት
ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት
ከምትገኝበት
ዋና የልቤ ትኩረት የዓይኔ ደግሞ ፍዘት
የጆሮዬ ጉጉት ድምፅህን ለመስማት
በእጅህ ለመነካት
በየዕለቱ ሙላኝ ልቤንም ለውጠው
በኢየሱስ የነበረውን ሀሳብ በእኔም ደግሞ ሙላ
በትላንቱ ሙላት ትዝታ መኖር አልፈልግም
ዛሬም ትሻሀለች ነፍሴ እንደ አዲስ
ከቶ አልለምድህም
እፈልግሀለሁ ፪x
በሙሉ ልቤ አንተን እሻሀለሁ
እፈልግሀለሁ ፪x
በሙሉ ኃይሌ አንተን እሻሀለሁ
እፈልግሀለሁ ፪x
በሙሉ ልቤ አንተን እሻሀለሁ
እፈልግሀለሁ ፪x
በሙሉ ኃይሌ አንተን እሻሀለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ