Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ማለዳ ማለዳ

Maleda Maleda

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ማለዳ (2x) ኦ አዲስ ነው ምህረቱ

ኦ አዲስ ነው ምህረቱ

መቼ ተጓደለ ኦ ፍቅሩ ቸርነቱ 2x

እንደ ማለዳ ጠል ምህረቱ ወረደ

የማይገባንን እኛን የወደደ 2x

ሰምቶ ለመነበት ብቸኛ መዳኛ 2x

ኢየሱስ ብቻ ነው የህይወት መገኛ 2x

እኔስ ለዘላለም ታማኝነቱን 2x

ቸርነት ምህረቱን ሰውን መውደዱን 2x

ለትውልድ ለዘመን ዛሬም እናገራለሁ 2x

ጆሮ ያለው ይስማኝ እግዚአብሔር ፍቅር ነው 2x

አቤት መታደል ነው በእግዚአብሔር መወደድ

አቤት እንዴት ውብ ነው በእግዚአብሔር መመረጥ

እራሱ ወዶ ወዶ አፅድቆ

እራሱ ወዶ ለክብሩ አብቅቶ

እራሱ ወዶ በቀኙ አስቀምጦ

ቸር አምላክ እግዚአብሔር ነው

ደግ አምላክ እግዚአብሔር ነው

ምህረት ለወደደ አይደለም ለሮጠ 2x

ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው እኛን ከወደደ 2x

እንዲሁ ያለ ምክንያት ምህረት ገኖልናል 2x

በኢየሱስ ምክንያት ከሞት አምልጠናል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ