Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
መሀሪነትህ — ኑኃሚን ተፈሪ

ባለማስተዋሉ ከቤትህ የራቀ

በገዛ ምኞቱ ተጠልፎ የወደቀ

ያ የጠፋው ልጅህ ዳግም ተመልሶ

በቤትህ ይኖራል ይቅርታህን ለብሶ

መሀሪነትህ ሩሩህነትህ

ስንቱን አቀፈ አጸና በቤትህ

ከሀጥያት እድፈት ከበደል ስህተት

ፍቅርህ ያድናል የትግስትህ ስፋት