Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ምህረቱን አይቼ ነው — ዳንኤል አምደሚካኤል

የጌታን ቸርነት ምህረቱን ሳስበው

መውጣቴ መግባቴ መኖሬ በእርሱ ነው

ለእኔ የበዛው ፍቅር እጅግ ይገርመኛል

ሁሌ ሳታቋርጥ አመስግን ይለኛል

እጆቼን ወደ ጌታ ወደ ኢየሱስ ዘርግቼ

አመሰግነዋለሁ ስለተዋቡት ቀኖቼ

ኢየሱስ ሕያው አለት የኔ ጽኑ መሰረት

ምሥጋና ይብዛህ እንጂ ምሥጋና አይነስበት