Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ምክር — ጌታያውቃል ግርማይ እና ብሩክታዊት አሰፋ

ከጉብዝናህ ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ አዎ ደስ ይበልህ

ውደዳት አፍቅራት እርሷን እንደራስህ

እህትህም ሚስትህም ባልንጀራህም ነች

እረዳትህ ሆና ለአንተ የተሰጠች (፪x)

በረከት ካገኘ ሚስትን ያገኘ ሰው

ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስ ከተሰጠ

እያመሰገነ ስለዚህ ስጦታ

ቤቱን በጽድቅ ይምራ ይንከባከባታል (፪x)