Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
መልክህን ጌታዬ — ተስፋዬ ጋቢሶ

መልክህን ጌታዬ ጸሃይ አክስሎታል

በሃሩሩ ብዛት ከስተህ ገርጥተሃል

ምቾትም ድሎትም አልነበረህም ጌታ

ለሰበዓዊው ፍጥረት በስቃይ ተመታህ (፪x)

የሞት ፅዋ ቀርባ ፈዋሼ ሲጨነቅ

የአባቱ ድምፅ ርቆት በጭንቀት ሲሳቀቅ