Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ምስክር ነኝ — ሳሙኤል ተስፋሚካኤል

ምስክር ነኝ እኔ አምላክ እንደሆንክ

ምስክር ነኝ እኔ ጌታ እንደሆንክ

እመሰክራለሁ እንደምትረዳ

ምስክር ነኝ እኔ እንደምትደርስ ለተጐዳ

እኔን ያዩ ዓይኖችህ ይባረኩ ለዘላለም

እኔን የሰሙ ጆሮዋችህ ይባረኩ ለዘላለም

እኔን ያነሱ እጆችህ ይባረኩ ለዘላለም

እኔን ያጽናኑ ቃሎችህ ይባረኩ ለዘላለም