Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
መተላለፌ ተደምስሶ — አዲስ አበባ መሠረተ ክርስቶስ መዘምራን

መተላለፌ ተደምስሶ እንደ በረዶ ነፅቻለሁ ተመልከተኝ

ሰይጣን እፈር በምን ትከሰኝ ይቅር ባይ አምላክ ይቅር ካለኝ

ና ልጄ ብሎ እንደገና ታርቆኛልና ፈጣሪዬ ጠንክሬአለሁ

አዲስ ሰው ሆኜ አገግሜአለሁ ጠላቴ ዋይ በል እኔ እስቃለሁ

አሳች ነህና ልታስተኝ ብዙ ለፋህ ክስ አመጣህ በአዕምሮዬ

ልትለየኝ ከፈጣሪዬ ምህረት ካገኘሁ ከጌታዬ