Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሞገሴ ነህ

Mogesie Neh

2015 · ትራክ 1 · 4:05 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሞገሴ ነህ ኢየሱሴ (፪x)

የማልተካው የማልተወው በሕይወቴ

ማዕረጌ ነህ ኢየሱሴ የእኔ ኢየሱሴ

የማልተካው የማልተወው በሕይወቴ

ዛሬ ላየኝ ላስተዋለኝ ሰው

እኔ አልለውም እጄ አንዳረገው

እናገራለሁ ጌታ ነው ብዬ

አልደብቀውም ኢየሱስዬን

እርሱ እኮ ነው ሞገስ የሆነኝ

ከአፈር አንስቶ ክብር ያሳየኝ

ታናሹን ሰው ሊያከብረኝ ወዶ

ቤቴ ገባ ከሰማይ ወርዶ

በዓይኖችህ ከታየሁኝ እኔ እጆችህ ከያዙኝ

ከዚህ ወዲያ በምን እሰጋለሁ

አንተን ይዣለሁ

አንተን ያስቀደመ ሰው

አይጐልም ከሚያስበው

ከዚህ ወዲያ በምን ይሰጋል

አንተን ይዞሃል

ሞገሴ ነህ ኢየሱሴ (፪x)

የማልተካው የማልተወው በሕይወቴ

ማዕረጌ ነህ ኢየሱሴ የእኔ ኢየሱሴ

የማልተካው የማልተወው በሕይወቴ

ምሕረቱ የረዳው ሰው

ቸርነቱ ሰው ያረገው

እኔ ነኝ ያ ሰው እኔ ነኝ

በፍቅሩ የታደገኝ

አቅም አጣሁ ጉልበቴ ጠፋ

እኔስ የለኝም የመኖር ተስፋ

ብሎ ለሚል ጌታ አለው መላ

ታሪክ ከፍቶ ያሳያል ሌላ

በዓይኖችህ ከታየሁኝ እኔ እጆችህ ከያዙኝ

ከዚህ ወዲያ በምን እሰጋለሁ

አንተን ይዣለሁ

አንተን ያስቀደመ ሰው

አይጐልም ከሚያስበው

ከዚህ ወዲያ በምን ይሰጋል

አንተን ይዞሃል

ሞገሴ ነህ ኢየሱሴ (፪x)

የማልተካው የማልተወው በሕይወቴ

ማረጌ ነህ ኢየሱሴ

የእኔ ኢየሱሴ

የማልተካው የማልተወው በሕይወቴ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ