Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ነፍሴን የሚያረካት

Nefsen Yemiyarekat

2022 · ትራክ 2 · 11:17 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ማን ተወኝ ማን ተቀየረ እያልኩኝ ሳዝን መኖሬ

አብቅቷል ልቤ በርትቷል ጌታ ኢየሱስ ስላለ ጐኔ

የማንም ፊት እንደቀድሞ ባይሆን ከእኔ ጋር

ሃሴት ከ'ኔ ጋር ነው መሽቶ ሲነጋ ፪*

ነፍሴን የሚያረካት ምሥጋና 'ሚሞላት ይሄ ነው

ነፍሴን የሚያረካት አምልኮ 'ሚሞላት ይሄ ነው

የአንተ ፊት ተቀብሎኛል እጅህ አቅፎኛል

<ጌታ ሆይ በአንተ ደስ ይለኛል > ፰*

ላይሰለጥንብኝ ልቤ ላይ ጨለማ

ፈገግ ካለልኝ የአንተ ፊት ከበራ

እረክታለች ነፍሴ በማትለወጠው

ሁልጊዜ ወደ አንተ ወደ አንተ ነው ማየው

የበራልኝ ፊትህ

ፈገግ ያለው ፊትህ

ጨለማዬን አሸንፏል

ጌታ በአንተ ደስተኛ ነኝ

ነፍሴን የሚያረካት ምሥጋና 'ሚሞላት ይሄ ነው

ነፍሴን የሚያረካት አምልኮ 'ሚሞላት ይሄ ነው

የአንተ ፊት ተቀብሎኛል እጅህ አቅፎኛል

<ጌታ ሆይ በአንተ ደስ ይለኛል > ፰*

ማን ተወኝ ማን ተቀየረ እያልኩኝ ሳዝን መኖሬ

አብቅቷል ልቤ በርትቷል ጌታ ኢየሱስ ስላለ ጐኔ

የማንም ፊት እንደቀድሞ ባይሆን ከእኔ ጋር

ሃሴት ከ'ኔ ጋር ነው መሽቶ ሲነጋ ፪*

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ