Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ነገ ለራሱ ይጨነቅ

Nege Lerasu Yichenek

ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከእኔ በላይ ለእኔ አሳቢ አለና

ከእኔ በላይ ለእኔ ጠባቂ አለና

አልጨነቅም እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነውና(X፪)

ነገ ለራሱ ይጨነቅ ነገ ከቶ አያሰጋኝም

ኢየሱስ በዋጋ ገዝቶኛል እኔ የራሴ አይደለሁም(X፪)

ሁሌ ከእኔ ጋራ አሃሃ

ጌታ ከእኔ ጋራ አሃሃ

ባልፍም በሸለቆ ወይም በተራራ(X፪)

የትላንትናው ሌት እንዲህ ያሳመመኝ

ለካ ለጥቅሜ ነው ሕይወት እንዲያምርብኝ

ከብርቱ ማሕበር ታግዬ ስወጣ

ጽናትን ብርታትን ሊሸልመኝ መጣ(X፪)

ሁሌ ከእኔ ጋራ አሃሃ

ጌታ ከእኔ ጋራ አሃሃ

ባልፍም በሸለቆ ወይም በተራራ(X፪)

ኦሆሆ እንዳንተ የለም አሄ እንዳንተ የለም(X፪)

ከእኔ በላይ ለእኔ አሳቢ አለና

ከእኔ በላይ ለእኔ ጠባቂ አለና

አልጨነቅም እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነውና(X፪)

ነገ ለራሱ ይጨነቅ ነገ ከቶ አያሰጋኝም

ኢየሱስ በዋጋ ገዝቶኛል እኔ የራሴ አይደለሁም(X፪)

ሁሌ ከእኔ ጋራ አሃሃ

ጌታ ከእኔ ጋራ አሃሃ

ባልፍም በሸለቆ ወይም በተራራ(X፪)

ለቅሶ ማታ ነበር ጥዋት አልቀጠለ

ማልዶ በመጣልኝ ጌታ ተሰበረ

አላለቅስም በቃ መከራው አለፈ

በህልውናው ውስጥ ልቤ ረሰረሰ(X፪)

ሁሌ ከእኔ ጋራ አሃሃ

ጌታ ከእኔ ጋራ አሃሃ

ባልፍም በሸለቆ ወይም በተራራ(X፪)

ኦሆሆ እንዳንተ የለም አሄ እንዳንተ የለም

አላለቅስም በቃ መከራው አለፈ

በህልውናው ውስጥ ልቤ ረሰረሰ(X፬)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ