Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ነገሩ ተገለበጠ — ሮማን ሳሙኤል

ተሳዳጅ እፎይ ሲል አሳዳጅ ሬሳበሬሳ

እግዚአብሔር ክንዱን ሲያነሳ

ጭንቅ ውስጥ አገባቸው አሳያቸው ፍዳ አበሳ

አንሸሽም ቢሉ የማይሆን ሆነ ነገሩ

ሠራዊቱ ታወከ መንከራኩሮቹ ታሰሩ

ባሕሩ ከደናቸው ደግሞ ሳይተያዩ

እስራኤል ተሻገረ ለዘለዓለም ተለያዩ[1]