ቅባትህ
Qebateh
አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቅባትህ በኔ ላይ ጌታ ሆይ በእጥፍ ይምጣ ቅባትህ በኔ ላይ
ቅባትህ በኔ ላይ ጌታ ሆይ በእጥፍ ይምጣ
በኢያሪኮ መንገድ ለወደቀው እንድደርስ
የኤልዛቤልን ግልሙትና እንዳፈርስ
ቅባትህ በኔ ላይ በእጥፍ ይምጣ
የተሰወረውን የጠላት አመጽ ይምታ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዘይት እንደሌላቸው ሌዋዊና ካህን
ቁስለኛውን እያዩ እንዳላዩ የሚያልፉትን
መሆን አልፈልግም በጎነት የሌለው
ቅባትህ ይምጣና ያንን ሰው ልታደገው
አዝማች · Chorus
ቅባትህ በኔ ላይ ጌታ ሆይ በእጥፍ ይምጣ ቅባትህ በኔ ላይ
ቅባትህ በኔ ላይ ጌታ ሆይ በእጥፍ ይምጣ
በኢያሪኮ መንገድ ለወደቀው እንድደርስ
የኤልዛቤልን ግልሙትና እንዳፈርስ
ቅባትህ በኔ ላይ በእጥፍ ይምጣ
የተሰወረውን የጠላት አመጽ ይምታ
ቁጥር 2 · Verse 2
በዝሙቷ ጉልበት ጎበዞችን የጣለች
የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያስካደች
እስከመቼ ድረስ ትሴስን ትቀመጥ
ልበቀላት ጌታ ቀባኝ ኤልዛቤል ትገልበጥ
አዝማች · Chorus
ቅባትህ በኔ ላይ ጌታ ሆይ በእጥፍ ይምጣ ቅባትህ በኔ ላይ
ቅባትህ በኔ ላይ ጌታ ሆይ በእጥፍ ይምጣ
በኢያሪኮ መንገድ ለወደቀው እንድደርስ
የኤልዛቤልን ግልሙትና እንዳፈርስ
ቅባትህ በኔ ላይ በእጥፍ ይምጣ
የተሰወረውን የጠላት አመጽ ይምታ
ቁጥር 3 · Verse 3
በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ ከፍቶ የተነሳ
የክንድህን ብርታት ክርስቶስን ሚያስረሳ
በስምህ መጽናቴን ጠላት አሁን ይወቅ
አሳቡን አልስትም እዋጋለሁኝ ይውደቅ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ