Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ቀን አለ — ተስፋዬ ጫላ

ያሰቡት ሳይሰምር ሲቀር ሆኖ እንደህልም

በእኩለ ቀንም ላይ በጊዜ ሲጨልም (፪x)

በዕድሜ ያከማቹት በዋዛ ሲበተን

በመከራ እሳት ማንነት ሲፈተን (፪x)

ሁኔታውን ሳይሆን ቃልህን አምናለሁ

ታድናለህ ብዬ ስንቴ ዘምሬያለሁ

ወጀቡ ቢበዛም በአንተ ተስፋ አልቆርጥም

ይዘንባል እላለሁ ደመናውን ባላይም