Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ታሪኬን የለዋወጥከዉ

Tariken yelewawetkewu

ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ታሪኬን የለዋወጥከዉ

ኑሮዬን አንዲህ ያዋብከዉ

ኤልሻዳይ ለዘላለም ነህና

ይብዛልህ አሁንም ምስጋና (x5)

ያልተገባኝ ሆኜ ሳለሁኝ

በአንተ ሞገስ አገኘሁኝ

ከፊትህ አልጣልከኝምና

ምህረትህ በእኔ ላይ ጸና (x2)

ታሪኬን የለዋወጥከዉ

ኑሮዬን አንዲህ ያዋብከዉ

ኤልሻዳይ ለዘላለም ነህና

ይብዛልህ አሁንም ምስጋና (x5)

ልዑል ሆይ እኔን አስበሃል

ለስምህ ክብር ይገባሃል

አስታወስክ ካለሁበት ስፍራ

እንዳልሞት ልብህ ለእኔ ራራ (x2)

ታሪኬን የለዋወጥከዉ

ኑሮዬን አንዲህ ያዋብከዉ

ኤልሻዳይ ለዘላለም ነህና

ይብዛልህ አሁንም ምስጋና (x5)

አቤቱ በአንተ ቸርነት

አገኘሁኝ ይህንን ነነት

ተመቸኝ ፍቅርህ የኔ ጌታ

ችላ አትተወኝ ለአንድ አፍታ (x2)

ታሪኬን የለዋወጥከዉ

ኑሮዬን አንዲህ ያዋብከዉ

ኤልሻዳይ ለዘላለም ነህና

ይብዛልህ አሁንም ምስጋና (x5)

ፈዋሼ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ

መች ጣልከኝ ጉያህ ሰበሰብክኝ

ዘመኔን ላንት ሰጥቻለው

ለክብርህ ሁሌ ዘምራለው (x2)

ታሪኬን የለዋወጥከዉ

ኑሮዬን አንዲህ ያዋብከዉ

ኤልሻዳይ ለዘላለም ነህና

ይብዛልህ አሁንም ምስጋና (x5)

ይብዛልህ አሁንም ምስጋና (x4)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ