ጠላት ዓይኑ እያየ
Telat Ayinu Eyaye
2005 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቃል ካፍህ ከወጣ አንተ ከተናገርህ
የማይሆን ምን አለ ትዕዛዝ ካወጣህ
የጨለመ ቢመስል ቀናት ቢቆጠሩም
ዘመኑን ጠብቆ መንጋቱ አይቀርም (፪x)
አዝማች · Chorus
በከፍታ ላይ ታቆማለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ
እራስን በዘይት ትቀባለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ
የተዘጋን በር ትከፍታለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ
አንደበትን በሳቅ ትሞላለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለአንተ ያልተቻለ ለአንተ ያቃተህ
ምንም ነገር የለም ለአንተ የሚሳንህ
ጠላት ምን ቢፎክር ለጥቂት ጊዜ ነው
ድንገት ስትነሳ አድራሻው ሲኦል ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
በከፍታ ላይ ታቆማለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ
እራስን በዘይት ትቀባለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ
የተዘጋን በር ትከፍታለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ
አንደበትን በሳቅ ትሞላለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አዋጅ ታውጆበት ሞቱን ሲጠባበቅ
ከሳሹ ሲፎክር ነፍሱ ስትጨነቅ
ድንገት ሳይታሰብ ታሪክ ተገልብጦ
ዛሬም ይዘምራል ከፍታውን ረግጦ (፪x)
አዝማች · Chorus
በከፍታ ላይ ታቆማለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ
እራስን በዘይት ትቀባለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ
የተዘጋን በር ትከፍታለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ
አንደበትን በሳቅ ትሞላለህ
ጠላት ዓይኑ እያየ ዲያቢሎስ ዓይኑ እያየ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ኢየሱስ ጌታዬ አምላኬ
ኢየሱስ ጌታዬ አምላኬ
ዛሬም አመልክሀለሁ ነገም አመልክሀለሁ
ዛሬም አመልክሀለሁ ክብር የአንተ ብቻ ነው
ዛሬም አመልክሀለሁ ነገም አመልክሀለሁ
ዛሬም አመልክሀለሁ ክብር የአንተ ብቻ ነው
ኢየሱስ ጌታዬ አምላኬ
ኢየሱስ ጌታዬ አምላኬ
ዛሬም አመልክሀለሁ ነገም አመልክሀለሁ
ዛሬም አመልክሀለሁ ክብር የአንተ ብቻ ነው
ዛሬም አመልክሀለሁ ነገም አመልክሀለሁ
ዛሬም አመልክሀለሁ ክብር የአንተ ብቻ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ