ትመለካለህ
Temelekaleh
2013 · ትራክ 1 · 6:36 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ገና ሰማይና ምድር ሳይፈጠር
ገና አማልክት የሚባል ሌላ ሳይኖር
ብቻህን በክብር ዙፋን ላይ ተቀምጠህ
ትመለካለህ! (፮x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ክብር የሚለው ቃል ማንም ሳይከብርበት
አንተ ክብር ለብሰህ ዘለዓለም ኖርክበት
መክበር የሚለው ቃል ሌላ ሳይከብርበት
አንተ ክብርን ጠግበህ ዘለዓለም ኖርክበት
ክብር ራሱ የሚያውቀው አንተን ነው
መጀመሪያ የታወቀው በአንተ ነው
ክብር ማለት የሚያውቀው አንተን ነው
መጀመሪያ የታወቀው በአንተ ነው
ክብር ራሱ የሚያውቀው አንተን ነው
መጀመሪያ የታወቀው በአንተ ነው
ትመለካለህ! እግዚአብሔር (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ኦሆሆ ! ኦኡዎ
ገና ፀሐይ ከዋክብት ሳይታሰቡ
ገና ነፋሳት ሳይወጡ ከመዛግብቱ
በአእላፋት መላዕክት ቀን ከሌት ተከበህ
ትመለካለህ (፮x)
አዝማች · Chorus
ክብር የሚለው ቃል ማንም ሳይከብርበት
አንተ ክብር ለብሰህ ዘለዓለም ኖርክበት
መክበር የሚለው ቃል ሌላ ሳይከብርበት
አንተ ክብርን ጠግበህ ዘለዓለም ኖርክበት
ክብር ማለት የሚያውቀው አንተን ነው
መጀመሪያ የታወቀው በአንተ ነው
ክብር ራሱ የሚያውቀው አንተን ነው
መጀመሪያ የታወቀው በአንተ ነው
ክብር ማለት የሚያውቀው አንተን ነው
መጀመሪያ የታወቀው በአንተ ነው
እናመልክሃለን! እግዚአብሔር (፯x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ