በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ
እነሆም ፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ ፥
ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ መልአኩም እንዲህ አላቸው
እነሆ ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ፤
ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና
ይህም ምልክት ይሆንላችኋል ፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ