Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
የነፍሴ እረፍቷ — ጆይፉል ሳውንድ

የነፍሴ እረፍቷ ደግሞም ጉብኝቷ ከሰማይ ነው

ከምድር ጭቃ አበጅቶኝ እስንፋሱን እፍ ሲልብኝ

ያን ጊዜ ሕያው ሰው ሆንኩኝ አገኘሁኝ ሕይወትን

ስጋዬ ቢሆን ከአፈር ነፍሴ ግን እስንፋሱ ነች

የምድር ከቶ ያልሆነች ከእግዚአብሔር የተገኘች

ስጋ ወደ አፈር ይሄዳል መገኛው ይሄው ነውና